ጠ/ሚ ዶክተር ዓብይ ከግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ከግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ ጋር ተወያዩ።

በግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ የተመራ የግብጽ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

በውይይታቸው ወቅትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ፥ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተላከ ደብዳቤን አስረክበዋል።