ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ከጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርኬል ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ። 

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ እንዳስታወቁት፥ መራሂተ መንግስት ሜርክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

መራሂተ መንግስቷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው በአፍሪካ እና በአውሮፓ ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ የጋበዟቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብዣውን መቀበላቸውን አረጋግጠውላቸዋል።(ኢቢሲ)