አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አዲስ አበባ ገብቷል

አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከዓመታት ስደት በኃላ ከሰዓታት በፊት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በርካታ አድናቂዎቹ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

እንዲሁም በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ዶክተር አምባቸው መኮነን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትም ተገኝተዋል፡፡

ታማኝ የበርካታ ሙያዎች ባለቤት ሲሆን የመድረክ አስተዋዋቂ፣ ቀላጅ፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች እና ተወዛዋዥ ነው፡፡ 

ወደ ሀገር ቤት መምጣቱን አስመልክቶ በርካታ ሰዎች በትዊተር መልዕክታቸው እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ይገኛሉ፡፡ 

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ትዊተር ላይ መልዕክታቸውን ካሰፈሩት መካከል አንዱ ናቸው፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹና ኢትጵያዊው ጀግና እንኳን ወደ ሀገር ገባህ በማለትም ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡(ኤፍ..)