ኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ቻይና በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ካለው የቻይና አፍሪካ ፎረም ጎን ለጎን ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በቆይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይና ቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት እድርገዋል።

ከውይይቱ በኋላም የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር ስምምነትቶችም ተፈራርመዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)