የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የ2010 የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆኑ

ፕሬዚዳንቱ ከ"እኔ ይልቅ ሌላው ይሻላል" በሚል መርህ ሌሎቹን የመንግስት ኃላፊዎች ከጎኑ አሰልፎ 'ቲም ለማን' በማዋቀር በወሰዱት የለውጥ እርምጃ ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ላደረጉት አስተዋጽኦ የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ሽልማት ተቀዳጅተዋል።

አቶ ለማ ሀገሪቱ ከፍተኛ ስጋት ላይ በነበረችበት ወቅት ሓሳብን ከተግባር ጋር በማዋሀድ ኢትዮጵያዊነት ዳግም እንዲለመልም አድርገዋል ተብሏል።

ከአቶ ለማ በተጨማሪም መምህራንን ጨምሮ በዘጠኝ ዘርፎች ለሌሎች የበጎ ሰው አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጥቷል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ለማ  መገርሳ የ2010 የበጎ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል ።(ኢዜአ)