ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ ቀጠናዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዲላሂ በኤርትራ አስመራ ተገናኝተው ተወያይተዋል። 

ሶስቱ መሪዎች በነበራቸው ቆይታም በተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዲላሂ የሶስቱን ሀገራት ቀጠናዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክር የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሶስቱ መሪዎች በደረሱት ስምምነት መሰረትም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በባህል፣ በማህበራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር የሚሰሩ ይሆናል።

መሪዎቹ አክለውም በኤርትራ እና በጂቡቲ መካከል ያለውን የድንበር አለመግባባት በውይይት ለመፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)