የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንጂነር ስመኘው በቀለ እራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ ።
የፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መግለጫው እንደገለጸው በሐምሌ 19 ፣ 2010 ዓም ጥዋት 2:30 ሰዓት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እንጂነር ስመኘው በቀለ በራሳቸው ሽጉጥ እራሳቸውን ማጥፋታቸውን የፎረንሲክ ምርመራ ውጤቱ እንደሚያሳይ ተገልጿል ።
እንጂነሩ የተኮሱት ጥይት በግራ ጆሯቸው ገብቶ በቀኝ ጆሮ አካባቢ የወጣ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ አደጋው ኢንጂነሩ ከሞቱ በኋላ በመኪናቸው ውስጥ ሁለት ፖስታዎች መገኘታቸው ተመልክቷል ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በመግለጫው ወቅት እንደተናገሩት እንጂነር ስመኘው ከመሞታቸው አንድ ቀን ቀደም ብለው ትልቅ ልጃቸው ማጥናት እንዳለበትና መረጃ መገኘቱን ገልጸዋል ።
በተጨማሪም ስመኘው ጠዋት ላይ ቢሮ መገኘታቸውና ለሁለት ሹፎሮቻቸውና ለጸሓፊያቸው ስልክ ጭምር በመደወል በፖስታ የታሸገ ማስታወሻ እንዲሰጥላቸው ማድረጋቸውን ያነሱት ኮሚሽነሩ ኢንጂነሩ በምን ምክንያት እንደሞቱ በትክክል የሚያስቀምጡ አለመሆናቸው ግን አያይዘው ገልጸዋል ።
እንጂነሩ በምን ምክንያት ሞቱ የሚለውን ለወደፊቱ ይበልጥ በዝርዝር ምርመራ የሚደረግበት መሆኑ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ የግድቡ ግንባታ በተፈለገው ደረጃ አለመድረስና እስካሁን የወጣው ወጪ ከፍተኛ መሆን እራሳቸውን ለማጥፋት ምክንያት እንደሆነ በጥርጣሬ አስቀምጠዋል ።