የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ዙሪያ የተረቀቀው አዋጅ ማሻሻያ ውይይት እየተደረገበት ነው

የህግ እና ፍትህ ማሻሻያ አማካሪ ጉባኤ ምክር ቤት የበጎ አድረጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ዙሪያ ያረቀቀውን የአዋጅ ማሻሻያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገበት ነው፡፡

ረቂቅ አዋጁ  የተለያዩ  መረጃ በማገላበጥ እና ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት የተዘጋጀ መሆኑን  በውይይቱ ወቅት ተገልጿል ።

በተለይም አዋጁ ገዳቢ የነበሩት እና ይነፍግ የነበረውን የመደራጀት ፣ የፈለጉትን ስራ የመስራት ተጨማሪ መስሪያ ቤት ለመክፈት ፍቃድ ያስፈልጋቸዉ የነበሩትን አዋጆች ያነሳ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዋጁ ተቀባይነት አግኝቶ በስራ ላይ ከዋለ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ አካላትን ነፃነት የሚያጎናፅፍ ይሆናል፡፡

በተለይም የበጎ አድራጎት ማህበራት እና ድርጅቶች በመብት ላይ እንዲሰሩ ለማድረግ በፈለጉት መንገድ ህብረተሰቡን በማደራጀት ያለምንም ገደብ ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ሥራ እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል ።