ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ከደቡብ ፕሬዚደንት ከሳልቫ ኪር ጋር በጽ/ቤታቸው እየተወያዩ ነው፡፡ መሪዎቹ በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና ሁለቱ የደቡብ ሱደን ተቀናቃኝ ሀይሎች የተፈራረሟቸው ስምምነቶች በፍጥነት ወደ ተግባር በሚሸጋገሩባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡ 
የደቡብ ሱዳን የመጨረሻውን የሰላም ስምምነትም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ዋንኛው ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻርን ጨምሮ ሌሎች ተፋላሚ ሀይላት ተፈራርመዋል።

በ 33ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ የተገኙት የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የመሪዎቹ ስብሰባ የተካሄደው የቀጠናው ሰላም ወደ ተሻለ ደረጃ በደረሰበት ወቅት መሆኑን አንስተው እንደነበር ይታወሳል።

እንዲሁም በትላንትናው የምሰራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ዶክተር አቢይ ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ቀወስ ዙሪያ ላበረከተው የሰላም ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበው ነበር።
(የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት )