የአፍሪካ ህብረት የአሰራር እና የመዋቅር የማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ በህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በስብሰባውም የህብረቱን ኮሚሽን አሰራርና መዋቅር ለማሻሻል ከዚህ ቀደም በአባል ሀገራት መካከል በተደረሰው መግባባት መስረት የቀረቡ የማሻሻያ አማራጭ ሃሳቦች ላይ ውይይት ተካሄዷል።(ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)