ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቡራዩ አካባቢ የተፈፀመውን ግድያ አወገዙ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት በቡራዩ አሸዋ ሜዳ፣ ከታ እና ፊሊ ዶሮ አካባቢ በንፁሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ።

ጥቃቱ በዜጎች አንድነት ላይ የተቃጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ መንግስት ይህን ጥቃት ባደረሱ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ድርጊቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪዎች ተጣርቶ ለህግ እንድሚቅርቡና ተመጣጣኝ ቅጣት እንድሚያገኙም ገልጸዋል።

የጸጥታ አካላትም ጉዳዩን በአስችኳይ እንዲያጣሩና ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አመራር ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።