ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሳውዲ አረቢያን ከፍተኛ ሽልማት ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሳውዲ አረቢያን ከፍተኛ የሜዳልያ ሽልማት ተሸለሙ ፡፡

ኢትዮጲያና እና ኤርትራ በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ባለ ሰባት ነጥብ ስምምነት ማድረጋቸውም ታውቋል ፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎችም ጦርነቱ አብቅቷል በማለት ከዚህ በኋላ አዲስ በሆነ መንፈስም የሰላም፤የወንድማማችነትና የተጣመረ ግንኙነታቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ይፋ አድርገዋል ፡፡

ከዚህ ባለፈም መሪዎቹ ትልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ለመጀመርም ተስማምተዋል፡፡

የሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመራሮች በስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል ።(ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)