የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የባቡር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የመጀመሪያው  የኢትዮጵያ የባቡር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

 የመጀመሪያው  የኢትዮጵያ ጉባኤው ከመስከረም 7 እስከ 8 የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከተለያዩ አለም አቀፍ አማካሪዎች ጋር በመሆን ያዘጋጀው እንደሆነ ታውቋል፡፡

በጉባኤው ከአሜሪካ  ከደቡብ አሜሪካ አውሮፓ እስያ እና አፍሪካ የሚመጡ የካበተ ልምድ ያላቸው አልሚዎች  የባቡር ኩባንያዎች እና ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች  እንዲሁም የአየር ንብረት ፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተቋማት ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

ጉባኤው አልሚዎቹ መንግስት በባቡር ዘርፍ ወደፊት ከግል ዘርፉ ጋር በጣምራ ለመስራት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ ተቋማቱ ፍላጎት እንዲያሳዩ ይሰራል ሲል የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ለመንግስትም ልምድ ያላቸውን ኩባንያዎች ለማግኘት በር ከፋች እንደሚሆን ተገልጿል ። ( ምንጭ: የምድር ባቡር  ኮርፖሬሽን ያገኘነው  መረጃ ያመላክታል)