በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን አደጋ በመቃወም የተቃውሞ ሰለፍ ተካሄደ

በአዲስ አበባ  በቡራዩ ፣ በከታና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ሰሞኑን  በዜጎች ላይ የደረሰውን  የግድያ አደጋ   በመቃወም  የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች  በአዲስ አበባ  የተቃውሞ  ሰለፍ  አድርገዋል ።

ለታቃውሞ  የወጡት  የዘረኝነት ይቁም ፣ ፍትህ በቡራዩ ፣ ከታና ሌሎች  አካባቢዎች  በግፍ   የተገደሉ  ወንድሞችንና እህቶችን ፣ ፖሊስና መንግሥት እየደረሱልን አይደለም በሚል  መካሄዱን  ተሳታፊዎቹ  ገልጸዋል ።

ሰላማዊ ሰለፍ አድራጊዎቹ  የተለያዩ  መፈክሮችን  በመያዝ  በቤተ-መንግሥትና  ሌሎች አካባቢዎች  በመዞር  ጭምር ተቃውሞ እያሰሙ  ፍትህ እንዲሠጣቸው  እየጠየቁ  ይገኛሉ ።

አደጋውን ማድረስ  እጃቸው አለበት የተባሉት አካላትን መንግሥት በማጣራት እርምጃ  እንዲወስድ የአዲስ  አበባ  ከተማ  ምክትል  ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ  በሠጡት  መግለጫ  መናገራቸው  ይታወሳል ።