በሀገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥ እንዳይደናቀፍ ጥያቄዎች በሳለማዊ መንገድ ሊቀርቡ አንደሚገባ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር ገለጹ

በሀገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥ እንዳይደናቀፍ ጥያቄዎች በሳለማዊ መንገድ ሊቀርቡ እንደሚገባ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ለውጡ እንደዚህ ቀደም ለውጦች በጅምር እንዳይቀር ሁሉም የየበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ወጣቱ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችንም ሆነ ቅሬታዎች ሲገልጽ፥ ህግና ስርዓትን በተከተለና የሌሎችን መብት በማክበር ብቻ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ይህ ካልሆነ ብዙ መስዋትነት የተከፈለበት ለውጥ ከግቡ ሳይደርሰ ሊጨናገፈና ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስድ እንደሚችል ነው አቶ ዳውድ የተናገሩት።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሀገር የገባውም ልዩነትን ለማጥፋት እንዳልሆነ የገለጹት ሊቀመንበሩ የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ ልዩነቶች መኖራቸውንም አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ ልዩነቶን ለማጥበብ በተረጋጋ መንፈስና በሰከነ አካሄድ ውይይቶችን ማድረግ እደሚየስፈልግ ተናግረዋል ተናግረዋል።

ሰውን በመግደልና ንብረትን በማውደም ልዩነት ይሰፋል እንደሆነ እንጂ የማይጠብ መሆኑንም ያመላከቱት የግንባሩ ሊቀመነበር ይህንን አይነት ድርጊት መቼም ቢሆን ድርጅታቸው የማይደግፍና የማይቀበል መሆኑን አስገንዝበዋል።

አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው የተናገሩት የኦሮሞ ነጻነት ግናባር የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

እንደ አቶ ዳውድ ገለጻ አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው ሲሆን፥ የኦሮሞ ነጻነት ግናባር እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

መስዋትነት የተከፈለውም የሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበርና ለመስጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)