ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቡራዩ ከተማና አካባቢው ተፈናቅለው በመድሃኒዓለም  ትምህርት ቤት ተጠልለው  የሚገኙ   ዜጎች ጎብኝተዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉት ወቅት ተፈናቃዮቹ ስላጋጠማቸው አደጋና ስለተፈጸመው  ሁኔታ ለጠቅላይ ሚንስትሩ አስረድተዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም  ተፈናቃዮቹን ባጋጠማቸው ሁኔታና በደረሰባቸው አደጋ  እጅግ ማዘናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚህ ድርጊት ፈፃሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑና ድርጊቱን እንዳይደገም  መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል ።

ከቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ ቀያቸው በፍጥነት እንዲመለሱና  እንዲቋቋሙ  መንግሥት የበኩሉን  ድጋፍ እንደሚያደርግም  ቃል ገብተዋል።