ሰበር ዜና ፤ ኦህዴድ የቀድሞ አመራሮችን በክብር ሸኘ

ኦህዴድ  ለረጅም  ዓመታት በድርጅቱ ሲያገለግሉ የቆዩትን   አመራሮችን  በዛሬው ዕለት   በክብር ሸኘ ።

ኦህዴድ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው የቀድሞ  አመራሮች    በክብር  መሸኘቱን አስታውቋል ።

ድርጅቱ  ወጣት አመራሮችን ወደፊት ለማምጣት  ባቀደውና ሥራዎችን ማካሄድ ተከትሎ ነው  ዛሬ ለነባር አመራሮቹ  ሽኝቱን  ማካሄዱን ይፋ ያደረገው  ።

 

በክብር  የተሸኙት  የቀድሞ  የኦህዴድ  አመራሮች  የሚከተሉት  ናቸው ።

1 አቶ አባዱላ ገመዳ

2 አቶ ጌታቸው በዳኔ

3  አቶ ኩማ ደመቅሳ 

4 አቶ  ግርማ ብሩ

5 አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

6 አቶ ኢተፋ ቶላ

7 አቶ ድሪባ ኩማ

8 አቶ እሸቱ ደሴ

9 ተፈሪ ጥያሮ

10 አቶ ደግፌ ቡላ

11 አቶ ሽፈራው ጃርሶ

12 አቶ አበራ ኃይሉ

13 አቶ ዳኛቸው ሽፈራው

14 ወይዘሮ ጊፍቲ አባስያ