የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መቀየሩን አስታወቀ ።
ድርጅቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን ስያሜ ለውጥ በተመለከተ ውይይት በማድረግ ነው ውሳኔ ያስተላለፈው ።
ድርጅቱ በተያያዘ ቋሚ ኮሚቴው በፖለቲካ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚ አጀንዳዎች ትኩረት አድርጎ ውይይት አድርጓል ።
በዛሬው ዕለት በተነሱት የትምህርት ፣ የጤና ተደራሽነትና አገልግሎት አሠጣጥ አፈጻጸም ላይ የተለያዩ ሓሳቦች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል ።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዓመታት የጤና ተደራሽነት ላይ ጠንካራ የሆነ አፈጻጸም ታይቷል ተብሏል ።
ሆኖም በባለሙያና በመድሓኒት አቅርቦት ረገድ ሰፊ ክፍተት ታይቷል ያሉት ተሳታፊዎች የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሠጥቶ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል ።
የድንበር ወሰንን የተፈጠሩ ችግሮችን በተመለከተ በተሳታፊዎች ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ለማ ከሶማሌ ጋር የተከሰተው የወሰን ችግር የኮንትሮባንዲስቶች ሴራ መሆኑን አስረድተዋል ።
ከሶማሌ ክልል ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የተሻለ ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
ኦህዴድ የኦሮሞ ህዝብ የማንነት ጥያቄን ለመመለስም ታሪክ የማይረሳው መልካም ሥራ መሥራቱንና ለወደፊቱን የህዝቡን ጥያቄዎች በአጭርና በረጅም ጊዜ ለመፍታትም ድርጅቱን ጥረት እንደሚያደርግ ተገልጿል ።
ኦህዴድ ለወጠፊቱን በለውጥ ፈላጊ አመራሩ ጋር በመሆን በድርጅቱም ሆነ በአገሪቱ የተሻለ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ለውጦች እንዲመዘገቡ በርትቶ እንደሚሠራ በውይይቱ ተገልጿል ።
በኦሮሚያ ክልል የኦዲት አፈጻጸሙም ምን እንደሚመስል የቁጥጥር ሥራው ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነም በጉባኤው ተመክሮበታል ።