የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ዝያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መርጧል።
ፓርቲው በዛሬው እለት ባካሄደው ምርጫ፦
1 ዶክተር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር
2 አቶ ለማ መገርሳን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የተመረጡት ሊቀመንበሩ እና ምክትል ሊቀመንበሩ እስከ ቀጣዩ ጉባዔ ድረስ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አመራር ሆነው እንዲቀጥሎ ሾሟል ።
በተጨማሪም ጉባኤው የኦዴግ ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን በማካሄድ ዘጠኝ አባላትን መርጧል ።
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን የተመረጡት ዘጠኝ አባላት የሚከተሉት ናቸው ።
- ዶክተር አብይ አህመድ
- አቶ ለማ መገርሳ
- ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
- አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
- አቶ አዲሱ አረጋ
- አቶ ሽመልስ አብዲሳ
- አቶ ፍቃዱ ተሰማ
- ዶክተር ዓለሙ ስሜ