የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ድርጅታዊ ጉባዔውን ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ

ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) 9ኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ።

ከእሮብ ጀምሮ በጅማ ሲካሄድ የቆየው የኦዴፓ ድርጅታዊ ጉባኤ የፓርቲውን ስያሜ ፣የአርማ እና የመዝሙር መቀየሩን  አስታውቋል ። 

በተጨማሪም የፓርቲው  በዛሬው ዕለት  ባካሄደው የማጠቃሊያ ጉባኤ  የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ምክር ቤት የሚሳተፉ አባላት ምርጫን በማካሄድ  ተጠናቋል።

በጉባኤው  የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉበት ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ ታሪካዊ ነበር በማለት ገልጸውታል።

በተለይም አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የመጡበት፣ የስያሜ፣ የአርማ እና መዝሙር ለውጥ የተካሄደበት መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ሊቀመንበሩ የኦሮሞ ዴሞራሲያዊ ፓርቲ ህዝቡን ለማገልገል ከዛሬ ጀምሮ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ይግባልም ብለዋል።

በአዲስ መንፈስና ሀሳብ ለማገልገል የተነሳው ፓርቲው በፍቅርና በአንድነት  ህዝብን  ከመቼውም  ጊዜ በላይ  ለማገልግል  እንደሚሠራ  አስታውቀዋል።