13ኛው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ ድርጅታዊ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

በመቐለ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ 1 ሺህ 650 ሰዎች በድምፅና ያለ ድምፅ ይሳተፉበታል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉበትም ይጠበቃል።

ጉባኤው የኦዲት ሪፖርትን የሚያደምጥ ሲሆን፥ በ12ኛው ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች አፈፃፀምንም ይገመግማል።

ከዚህ በተጨማሪም በድርጅታዊ ጉባዔው ሀገራዊ ሁኔታውን ከድርጅቱ እና ከትግራይ ህዝብ አንፃር የሚመለከት መነሻ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

የድርጅቱን ህገ ደንብ ለማሻሻል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ተወያይቶም ውሳኔ ያሳልፋል፣ ውሳኔ በማሳለፍም እና የቀጣይ ዓመታት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥም ከጉባኤው ይጠበቃል።

“የአንድነትና የፅናት ጉባኤ ለህዳሴያችን” በሚል ስያሜ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፥ ህዝባዊነታችን ለጽናታችንና ድላችን መሠረት ነው የሚል መሪ ቃል ያለው መሆኑም ተጠቅሷል።

በዚሁ ጉባኤም የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ይመርጣል ተብሎም ይቀጠበቃል ።(ኤፍቢሲ)