የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ከዛሬ ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በዛሬው እለት የሚጀምረው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ እስከ መስከረም 21 2010 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድም ድርጅቱ አስታውቋል።

በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ በሀገሪቱ ያለውን የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችሉ  ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበትም ደኢህዴን ገልጿል።

እንዲሁም ሀገራዊ ለውጡን በብቃት እንዲሳካ ማድረግ፣ የንቅናቄው የቀደሙ ጉባኤዎች ውሳኔዎች አፈፃፀም  በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥም የጉባዔው አጀንዳዎች ናቸው።

ደኢህዴን ያስጠናቸው የለውጥ መሠረታዊ እቅዶች ላይ ምክክር የሚደረግ ሲሆን፥ በፖርቲ ግንባታ ጥናት ስር የአርማ የስያሜና የህገ ደንብ ጉዳዮች ላይ ጉባሄው ይወያያል ነው የተባለው።

በተጨማሪም በድርጅታዊ ጉባዔው የንቅናቄውን ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ይካሄዳል።

በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባሄ ላይ ከ1 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 800 በድምፅ እንደሚሳተፉም ተገልጿል።