ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አሰናበተ

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ ሽፈራው ሽጉጤን እና ሲራጅ ፈጌሳን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ።

ደኢህዴን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

2.አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

3. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ

4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

5. አቶ ተክለወለድ አጥናፉ

6. አቶ ሳኒ ረዲ

7. አቶ ታገሰ ጫፎ

8. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

9. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም

10. አቶ ደበበ አበራ

11. አቶ መኩሪያ ሀይሌ

12. አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ

13. አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ

14. አቶ ተመስገን ጥላሁን

15. አቶ ወዶ ኦጦ

16. አቶ ያዕቆብ ያላ

17. አቶ ሰለሞን ተስፋዬ

18. አቶ ፀጋዬ ማሞ

19. አቶ ንጋቱ ዳንሳ

20. አቶ አድማስ አንጎ

21. አቶ ኑረዲን ሀሰን

22. አቶ ሞሎካ ወንድሙ

23. አቶ አብቶ አልቶ ናቸው ከማእከላዊ ኮሚቴው በክብር የተሰናበቱት።

ከማእከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱት አባላት ከ15 እስክ 17 ዓመታት በተለያየ የሀላፊነት ደረጃ ያገለገሉ መሆናቸውም ተገልጿል።

ጉባዔው በተጨማሪም ከድርጅቱ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አቶ ካሚል አህመድን በክብር አሰናብቷል።

እንዲሁም እስከ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በእግድ እንዲቆዩ አድርጓቸው የነበሩ አባላትንም አሰናብቷል።

በዚህም መሰረት፦

1. ወይዘሮ አማረች ኤርሚያስ

2. አቶ ሳሙኤል ደምሴ

3. ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ከድርጅቱ ተሰናብተዋ ል።