አቶ ደመቀ መኮንን በአዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመቀጠል ተስማሙ

አቶ ደመቀ መኮንን ስያሜው ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በቀየረው ድርጅት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲቀጥሉ ከድርጅታዊ ጉባዔው የቀረበውን  ሀሳብ ተቀብለው ለመጠቀል  መስማማታቸውን አስታውቀዋል ።

ድርጅታዊ ጉባዔው  እያደረገ ባለው ውይይት ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት  ምርጫ ባይወዳደሩ ብሎ ለጉባኤ ጥያቄ  ባቀረበባቸው 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የቀረበውን መነሻ ተቀብሎ እንዲፀድቅ አድርጓል ።

የ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ  ተሳታፊዎች አቶ ደመቀ  መኮንን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመልቀቅ የቀረበውን ሓሳብ  በከፍተኛ ደረጃ  በመቃወማቸውን ተከትሎ ነው  አቶ ደመቀ መኮንን  በአባልነት  ለመቀጠል የተስማሙት ።

ሆኖም  በድርጅታዊ ጉባዔው  ሌሎች ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን የቀድሞ 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሰናበቱ የቀረበውንመነሻ ሓሳብ ተቀብሎ አፅድቋል።

የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴው  በትምህርት፣ በአምባሳደርነት እና በክብር የሚሰናበቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝርን እንደሚከተለው አቅርቧል  

በክብር የሚሰናበቱ ነባር  አመራሮች

1 አቶ ከበደ ጫኔ

2 አቶ መኮንን የለውምወሰን

3 ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው

4 አቶ ጌታቸው አምባዬ ናቸው

በትምህርት ምክንያት  ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት  እንዲሰናበቱ የቀረቡት  

1 አቶ ዓለምነው መኮንን

2 አቶ ለገሰ ቱሉ

3 አቶ ጌታቸው ጀምበር

4 አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ

5 አቶ ደሳለኝ አምባው

6 ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ ናቸው ።

በተጨማሪም  በአምባሳደርነት እያገለገሉ ከሚገኙት  የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ  አባላት  ውስጥ  

1አቶ ካሳ ተክለብርሃንና

ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ  በቀጣይ  ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዳይወዳደሩ የቀረቡ ናቸው

ድርጅታዊ በዛሬው ዕለትም  ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፥ የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫን አካሂዶ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል