ህወሓት ዶክተር ደብረፅዮንን የድርጅቱ ሊቀመንበር ወይዘሮ ፈትለወርቅን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ እያካሄደ ባለው ጉባኤ ዶክተር ደብረፅዮንን የደርጅቱ ሊቀመንበር ወይዘሮ  ፈትለወርቅን ገብረእግዚአብሄርን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መምረጡን  አስታውቋል  ።

በተጨማሪም ጉባኤው የህወሓት እና የኢህአዴግ ስራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል።

ህወሓት ለኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚነት የመረጣቸው አባላት የሚከተሉት ናቸው ።  

1. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር

3. አቶ ጌታቸው ረዳ

4. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

5. ዶክተር አብረሃም ተከስተ

6. ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም

7. አቶ ጌታቸው አሰፋ

8. ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ

9. አቶ ዓለም ገብረዋህድ  ናቸው ። 

ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ከተመረጡት ዘጠኝ አባላት  በተጨማሪም ሁለት አባላትን በማከል በአጠቃላይ 11   አባላት ያሉት የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም ተመርጠዋል ።

ሁለቱ ተጨማሪ ሁለቱ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ናቸው:

10. አቶ በየነ መክሩ

11. ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል ናቸው።