ኢህአዴግ በድርጅታዊ ጉባዔው የሀገሪቱን አንድነትና ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አቅጣጫ ያስቀምጣል – ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የሀገሪቱን አንድነትና ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እምነቴ ነው ሲሉ የደኢህዴን ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል ገለጹ።

ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ በተጀመረው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የመክፈቻ ንንግር ያደረጉት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ለተሳታፊዎቹ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ደኢህዴን በታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ወቅት የሚካሄደውን ይህንን ጉባዔ በማዘጋጀቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት ደኢህዴን የህዝቦች ትስስር ለሁለተናዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል ባለፉት አምስት ቀናት ያካሄደውን ጉባዔ በስኬት በተጠናቀቀበት ማግስት የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ለውጡን የሚያስቀጥል ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተናግራዋል።

ጉባዔው የሀገሪቱን አንድነትና ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር፣ በሂደቱ የነበሩ ጥንካሬዎች አጎልብቶ ለመቀጠልና ድክመቶችንና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣትና የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ወደ አንድ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚያሽጋግሩ አቅጣጫዎች የሚያስቀምጥ ጉባዔ እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል።

ሊቀመንበሯ ይህ ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)