“ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች”- የኢህአዴግ ሊቀመንበር ክቡር አብይ አህመድ

የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች የእራት ግብዣ ባደረጉበት ወቅት  ዶክተ አብይ አህመድ እንደተናገሩት ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሳጣለች በማለት  ተናግረዋል ። 

የንግዱ ማህበረሰብ ባዘጋጀው በዚህ የእራት ግብዣ ወቅትም  ለኢህአዴግ  ሊቀመንበር ክቡር ዶክተ አብይ አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት 40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የሰባት ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል።

ዶክተ አብይም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ: ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች" ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት በጥሩ ምሳሌ  ገልጸዋል።

በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት አድርገዋል።