የጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ጉባዔ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

የጨፌ ኦሮሚያ አራተኛ ዓመትሦስተኛ አስቸኳይ ጉባዔ  ዓዋጆችንና  ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል።

ጉባዔው ወይዘሮ ሎሚ በዶ የጨፌው አፈ ጉባዔ አድርጎ የሾመ  ሲሆን፣ የቀድሞውን አፈ ጉባዔ አምባሳደር እሸቱ ደሴ ተክተው ዛሬ ሥራ ጀምረዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  ተሿሚዎችን ለጉባዔተኞቹ  ሲያቀርቡ የክልሉ መንግሥት ለውጡን ወደፊት ለማራመድና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ብቃትና አቅም ያላቸውን አመራሮች መመደቡን ገልጸዋል።

የክልሉን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለስራ አመቺ በሚሆን  መልኩ በሦስት ክላስተሮች ተከፍለው በምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲመሩ መደረጉን   አስረድተዋል።

በዚህም መሠረት

  1. ወይዘሮ ጠይባ ሐሰን የማህበራዊ ክላስተር ምክትል ፕሬዚዳንት
  2. ዶክተር ግርማ አመንቴ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የግብርና ክላስተር ኃላፊ
  3. አቶ አህመድ ቱሳ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፤

በተመሳሳይ

  1. አቶ አሰግድ ጌታቸው የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
  2. ወይዘሮ ሙና አህመድ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣
  3. አቶ አድማሱ ዳምጠው የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣
  4. ዶክተር ገረመው ሁሉቃ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፣
  5. አቶ ጥላሁን ወርቁ የኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ፣
  6. ዶክተር ኢንጅነር ፍቃዱ ፉፋ የከተሞች ልማትና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ፣
  7. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ፣
  8. አቶ ኤባ ገርባ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ፣
  9. አቶ ሙላቱ ፅጌ የንግድ ቢሮ ኃላፊ፣

10.ወይዘሮ ፈቲያ መሐመድ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣

11.ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፣

  1. አቶ ዳባ ደበሌ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ፣

13.አቶ ተሾመ ግርማ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መሥሪያ ቤት ዋና ዐቃቤ ህግ ሆነው ተሹመዋል።

ተሿሚዎቹ ለሹመት የቀረቡት ባላቸው የትምህርት ዝግጅት ፣ በስራ ታታሪነትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑም  ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።(ኢዜአ)