የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የሚያደርጉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩና የተለያዩ የሁለትዩሽ ስምምነቶች እንደሚፈራረሙም ይጠበቃል።

የጁሴፔ ኮንቴ ጉብኝት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከአውሮፓ ሃገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሳደግ የያዙት እቅድ አካል ነው ተብሏል።