የስሎቬንያው ፕሬዚዳንት ቦርት ፓሆር በመጭው ሰኞ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

የስሎቬንያ ፕሬዚዳንት ቦሩት ፓሆር ከመጭው ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ ።

ፕሬዚደንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

በተጨማሪም ፕሬዚደንት ቦሩት በቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

የስሌቬንያ  ፕሬዚደንት ጉብኝት የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር ያለውን የጋራ ፍላጎት እንደሚያሳይም ተመልክቷል ።(ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)