በሰው ዘቅዝቆ መስቀል ወንጀል ከተጠረጠሩት 14 ግለሰቦች 6ቱ ክስ ተመሰረተባቸው

በሻሸመኔ ከተማ በሰው ዘቅዝቆ መስቀልና መግደል ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩ 14 ግለሰቦች በስድስቱ ላይ ክስ መመስረቱን የከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መኮንን ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በወንጀሉ ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ስድስቱ ላይ አቃቢ ህግ በቂ ማስረጃ በማግኘት ነው ክስ ሊመሰረትባቸው የቻለው፡፡

በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተጨማሪ ቀጠሮ በመስጠት ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ አሳልፏል፡፡

ተጠርጣሪዎች ነሀሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም በነበረው የአክቲቪስት ጀዋር መሀመድ የአቀባበል ስነ ስርአት ሻሸመኔ ከተማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ዘቅዝቀው በመስቀል ለሞት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡