ምክር ቤቱ አቶ ታገሰ ጫፎን አፈ-ጉባዔ አድርጎ ሾመ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሰ ጫፎን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ በማድረግ ሾሟል ። 

አቶ ታገሰ ጫፎ ከዚህ ቀደም ከዞን አንስቶ በክልልና በፌዴራል ደረጃ በተለያዩ የአመራርነት እርከኖች አገልግለዋል፡፡

የምክር ቤቱ ብቸኛ እጩ የነበሩት አቶ ታገሰ  በሙሉ ድምጽ በመመረጣቸው በምክር ቤቱ ደንብ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሆነዋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈጉባዔ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን በመተካት ነው አቶ ታገሰ እንዲሾሙ ያደረገው ።