የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ከ11 ወደ 9 ዝቅ አደረገ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን ከአሥራ አንድ ወደ ዘጠኝ ዝቅ አደረገ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥሩን ቀደም ሲል ወደነበረበት የቀነሰው።

በድርጅቱ ህገ-ደንብ መሰረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን የመጨመርም ሆነ የመቀነስ ስልጣን የድርጅታዊ ጉባኤ ነው።

ቀደም ሲል ማዕከላዊ ኮሚቴው የሥራ አስፈጻሚ  አባላትን ቁጥርን ከዘጠኝ ወደ 11  ከፍ ሲያደርግ በድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔ አለመሆኑም ለማስተካከያ ውሳኔው መነሻ እንደሆነ ተመልክቷል።

ድርጅቱ በቅርቡ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጡ ይታወሳል።

በምርጫው  መሰረትም፦ 

  1. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
  2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
  3. አቶ ጌታቸው ረዳ
  4. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ
  5. ዶክተር አብረሃም ተከስተ
  6. ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም
  7. አቶ ጌታቸው አሰፋ
  8. ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ
  9. አቶ ዓለም ገብረዋህድ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው  መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን፥ እነዚህን ጨምሮ አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል የተካተቱበት የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትንም መርጦ ነበር። (ኤፍ.ቢ.ሲ)