ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ  ተገለጸ ፡፡

ሥልጠናውን ንግግር በማድረግ የከፈቱት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስልጠናው አመራሩ ለውጡን ለማስቀጠል የማያቋርጥ የመማርና የማድረግ ሂደት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

አመራሩ ለሚመራው ሠራተኛም ሆነ ህዝብ ምሳሌ መሆን እንዳለበት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰዓት በማክበር፣ በትጋት በመስራት፣ ውጤታማ በመሆን እንዲሁም በሌሎች ህዝቡን በሚጠቅሙ መልካም ተግባራት ምሳሌ ሆኖ ማሳየት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

እያንዳንዱ ሚንስትር የመጀመሪያ 100 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ፈጣንና የህዝቡን ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ ለማምጣት እንዲረባረብ በንግግራቸው አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው በተመረጡ የዘርፉ ምሁራን በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ እና በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊቴር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡