የትግራይ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የቀረቡ የቢሮ ሃላፊዎችን እና የዞን አስተዳዳሪዎችን ሹመት አጸደቀ።

የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 5ኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤው በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የቀረቡ የቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ዶክተር አብርሃም ተከስተ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ

አቶ ቴድሮስ ገብረእግዚአብሄር – የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ

ወይዘሮ ሊያ ካሳ – የክልሉ የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ

ወይዘሮ ገነት አረፈ – የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ

ወይዘሮ አሰፉ ሊላይ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

አቶ ተኪኡ ምትኩ – የክልሉ የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

ወይዘሮ አልማዝ ገብረፃድቅ – የክልሉ የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን – የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

ዶክተር ፀጋ ብርሃነ – የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ቢሮ ሃላፊ በመሆን በዛሬው የምክር ቤቱ ውሎ ተሹመዋል።

በተጨማሪም ለዞን ዋና አስተዳዳሪነት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እጩዎችን አቅርበው ምክር ቤቱ አጽድቆታል።

በዚህ መሰረት

አቶ እያሱ ተስፋይ – የትግራይ ማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አቶ ረዳኢ ሃለፎም – የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አቶ ርስቁ አለማው – የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል።

ሹመቱ የተሿሚዎችን የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ልምድ እና የፖለቲካ ብቃት መሰረት ያደረገ መሆኑም በዚህ ወቅት ተገልጿል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)