ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያውን ጉዙ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ አቅንተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑት ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው።

በጁባ ጃን ጋራንግ አደባባይ በሚካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተፋላሚ ኃይሎች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኬንያ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ንግግር እንደሚያደርጉ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።