ለቀናት ጉባኤውን በሃዋሳ ሲያካሂድ የቆየው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለው የክልሉ መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሰረት አዳዲስ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፦
- አቶ ወንድሙ ገብሬ፦ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ታምራት ዲላ፦ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ኑሪዬ ሱሌ፦ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኃላፊ
- አቶ ጥላሁን ከበደ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ
- ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፦የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አብርሀም ማርሻሎ ፦ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ክፍሌ ገ/ማሪያም ፦ በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አንተነህ በፍቃዱ ፦የውሀ ማእድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ፦ በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አቅናው ካውዛ ፦ የጤና ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አክሊሉ ለማ ፦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ
- ወ/ሮ አስቴር ከፍታው ፦የሴቶች ፥ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ፦ የኢንተርፕራይዞችና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ንጉሴ አስረስ ፦ የገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ
- ወ/ሮ ሰብለ ፀጋ ፦ የባህል ፥ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ኤልያስ ሽኩር ፦ ም/ር/መስተዳደርና የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ሀልገዮ ጂሎ ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- ዶ/ር ሃሚድ ጀማል ፦ የእንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱን በአፈ ጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ መልቀቂያን በመቀበል በምትካቸው ወይዘሮ ሄለን ደበበን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል። (ምንጭ የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ)