የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ተቋቋመ

አደረጃጀቱ  በጠቅላይ  ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሥር  የሆነና  የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሥራን ተክቶ የሚሠራ የፕሬስ  ሴክረቴሪያት ተቋቋመ ።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያትን ለማስተዋወቅ  በተዘጋጀው  መርሃ ግብር ላይ  እንደተገለጸው  አቶ ሽመልስ አብዲሳ  በሚኒስትር  ማዕረግ የጠቅላይ  ሚንስትር ጽህፈት  ቤት  ኃላፊ  በመሆን ተሾመዋል ።  

በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ሥር  በተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬተሪያትም  ወይዘሮ ቢልለኔ ስዩም  በኃላፊነት  ተሾመዋል ።

የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ወይዘሮ ቢልለኔ ስዩም በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን  የመጀመሪያው  ቀን መግለጫቸውን  ሠጥተዋል ።

ወይዘሮ ብልለኔ  በመግለጫው እንደጠቆሙት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን  ጽህፈት ቤት  መታጠፉንና  አዲስ የተቋቋመው  ሴክሬተሪያት  መረጃን  በግልጽ ለመሥጠትና  ከሚዲያው ጋር ያለውን ግንኙነት   ለማሳደግ  የሚሠራ  ነው ብለዋል ።

የፕሬስ  ሴክሬተሪያቱ  በተለያዩ  ባለሙያዎች  የተደራጀና  የዳበረ  እንደሚሆነው ይሠራል  ብለዋል ።

የህዝብ ተወካዮች  ምክርቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች  ጽህፈት ቤት ታጥፏል በምትኩም  በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሥር  የተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊነቱን ወስዶ ሥራውን መጀመሩን ወይዘሮ ቢልለኔ ገልጸዋል ።

ሴክሬተሪያቱ  ከተለያዩ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና ከተለያዩ የክልል መንግሥታት ጋር በመሆን  ወቅታዊና ትክክለኛ  መረጃን  ለህብረተሰቡ  የመሥጠት ኃላፊነት  ተጥሎበታል ብለዋል ።

የፕሬስ  ሴክሬተሪያቱን አሠራርና አወቃቀር በተመለከተ በቀጣይ በሚሠጥ መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን  የሚገለጽ መሆኑንም  ወይዘሮ ቢልለኔ ጠቁመዋል ።

ክቡር  ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ለመገናኛ ብዙሃን በተሻለ መልኩ መረጃን ለማቅረብ  ቃል በገቡት መሠረት  በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣነ የተመዘገቡ  ጋዜጠኞች  ቋሚ የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት  መግቢያ ተዘግጅቶላቸው  መግለጫዎችን የሚያተፉበት ምቹ ሁኔታ ም መፈጠሩን ወይዘሮ ቢልለኔ አስረድተዋል ።