ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ትናንት እለት በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አድርገዋል ።

የካናደው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎም በአሁኑ ወቅት  በሴቶችን በቁልፍ የመንግስት አመራር ቦታዎች መሳተፍ መንግስታቸው  ማድነቁን ገልጸዋል ።

የካናዳ መንግሥት ይህንን በሙሉ ልብ ለመደገፍና ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ገልፀውላቸዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የመጣውን ለውጥ በኋላም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ መድረክ እየተጫወተች ያለውን ሚና ጠቃሚ  መሆኑን ተናግረዋል ።

በስልክ ውይይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በቅርቡ ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ለጠቅላይ ሚንስት ዶክተር አብይ ገልጸዋል ።(ምንጭ:  የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)