በመዲናዋ ቦታዎችን አጥረው ንብረታቸውን በተሠጣቸው የጊዜ ገደብ ባላነሱት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ጊዜ ታጥረው የቆዩ ቦታዎች የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት ንብረታቸውን በተሠጣቸው የጊዜ ገደብ ባላነሱት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ።     

የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ንብረታቸውን እንዲያነሱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው 144 አልሚዎች መካከል 14ቱ እስካሁን ንብረት አላነሱም።

በመሆኑም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ንብረታቸውን ካላነሱ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

ንብረታቸውን እንዲያነሱ ከተነገራቸው አልሚዎች መካከል የአስተዳደሩን ውሳኔ ወዲያውኑ በመቀበል አብዛኞቹ እንዳነሱ የተገለጸ ሲሆን የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እና መከላከያ ሚኒስቴር ይገኙበታል።

የተመለሱት መሬቶች ለግለሰቦች እየታደለ ነው የሚል የተሳሳተ መረጃም በህብረተሰቡ ዘንድ እየተሰራጨ መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው፥ ለማንም የተሰጠ መሬት እንደሌለ አስታውቋል።(ምንጭ:የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)