የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በዛሬው  ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በምዕራባዊ ትግራይ በኩል ባታር በተሰኘው አካባቢ ከአገር ለመውጣት ሲሞክሩ  ነው በህብረተሰቡ እና በመከላከያ ኃይል ትብብር የተያዙት፡፡

ጀነራሉ በቁጥጥር  ሥር ውለው  በአሁኑ ወቅት ወደ አዲስ አበባ እየመጡ መሆኑም ተገልጿል ።

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን( ሜይቴክ) ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወቃል።

የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ  በትናንትናው  ዕለት  በሠጠው  መግለጫ  ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በመፈፀማቸው የተጠረጠሩ 27 ከፍተኛ የሜቴክ አመራሮች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ይታወቃል፡፡