11ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይጀመራል

11ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ በዛሬው  ዕለት የሚጀመር መሆኑ ተገለጸ  ።

ጉባኤው ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፥ ትኩረቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን በማሻሻል እና ህብረቱን ከእርዳታ ጥገኝነት ለማውጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል  ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባውም ላይም ከ45 ሀገራት በላይ መሪዎች እንደሚሳተፉም ነው የተገለጸው ።