በሀገር ደረጃ የተጀመረውን ለውጥ በአፋር ክልል ለማሳካት የአብዴፓ አመራሮች በአዲስ እንዲተኩ ከስምምነት ላይ ተደረሰ

በሀገር ደረጃ የተጀመረው ለውጥ በአፋር ክልል ይበልጥ እንዲሳካ ለማስቻል ነባር የአብዴፓ አመራሮች በአዲስ እንዲተኩ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ጋር ባለፈዉ ሳምንት የጀመሩትን ዉይይት ዛሬም ቀጥለዋል።

ዉይይቱ በአገር አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በክልል ደረጃ እንዴት መካሄድ እንዳለበት ትኩረቱ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ በበለጠ በማጠናከር ህዝቡ የልማት ተጠቃሚነቱን የበለጠ ለማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም አመራር በጋር ለመስራት ተስማምተዋል። 

በሌላ በኩል የክልሉን ወጣቶች ይበልጥ በማሳተፍ የህዝቡን የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ለመመለስ አመራሮቹ ቃል መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።