በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ፣የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 2ኛው የኢጋድ አባል አገራትና ሩዋንዳ የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በመኮንኖች ክበብ ተካሂዷል ።
ከወር በፊት የተካሄደው የመጀመሪያው የኢጋድ አባል አገራት የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ ሩዋንዳ በተሳተፈችበት የደቡብ ሱዳንን ወቅታዊ ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይን የሚከታተል የቴክኒካል ኮሚቴን ማቋቋሙ ይታወሳል ።
አዲስ አበባ እየተካሄደው ባለው ስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚ ኃይሎች ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል ።
እንደ ኢንጂነር አይሻ ገለጻ የደቡብ ሱዳን ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል ።
የኢጋድ የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ በዛሬ አጀንዳውም የተቋቋመው የቴክኖካል ኮሚቴ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራትም ላይ ውይይት እየተደረገ ሲሆን የደቡብ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል ።