በአገሪቱ ያለውን ለውጥ ሠራዊቱ የሚደግፈው መሆኑ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ  ሠራዊቱ  የሚደግፈው  መሆኑን  የአገር መከላከያ  ሚኒስቴር  አስታወቀ ።

በሚኒስቴሩ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ በዛሬው  ዕለት  መግለጫ  ሠጥተዋል ።

ሜጀር ጄነራል በመግለጫቸው እንደገለጹት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ  ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ  አካላትም  ካሉ  መከላከያ  ህገመንግሥቱን  መሠረት  በማድረግ   አስፈላጊውን  እርምጃ ይወስዳል ብለዋል ።

መከላከያን  ከሜቴክ ጋር  በማገናኘት በሠራዊቱ  ላይ  እየተካሄደ  ያለውን  የስም ማጥፋት ዘመቻን  እንደሚያወግዙት  ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተናግረዋል ።