ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመንግሥታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም አካባቢያዊ ቢሮ ተወካይ ጋር ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከአካባቢያዊ ቢሮ ተወካይ ጋር በኢትዮጵያ በሚካሄደው የለውጥ ሂደት ላይ ነው የመከሩት፡፡  

በዚህም ከለውጥ ሂደቱ ጋር በተያያዘ ተቋሙ አስተዋጽዖ ማበርከት በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ በተጨማሪ ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በቀድሞው የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እና በኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተቋቋመው የአየር ንብረት ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።( ምንጭ: ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት )