ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ጋር ወይይት አደረጉ

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር ውይይት  አደረጉ ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ ጋር በትናንትናው ዕለት ተገናኝተው ተወያይተዋል ።

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍርድ ቤቱ ጋር የፍትህ የበላይነትንና የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በሚሠሩ የማሻሻያ ተግባራት ዙሪያ  በትብብር  ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።

ፍትህን በዘላቂነት ማረጋገጥ ልማትንና የህብረተሰብ ለውጥን ማረጋገጥ ማለት እንደሆነ የጠቆሙት ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፥ አስፈጻሚ አካላት ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖራቸውና የህግ የበላይነት እንዲከበርም የከተማ  አስተዳደሩ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን በአንክሮ ተናግረዋል፡፡ (የአዲስ  አበባ ከተማ  ከንቲባ  ፅህፈት ቤት)