ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ከኳታሩ አሚር ሼክ ቢን ሀመድ አል አሳኒ ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት ከኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀመድ አል -አሳኒ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸው  ተገለጸ ።

ሁለቱ  መሪዎች  በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ኳታር ትብብርና ግንኙነትን ይበልጥ ለማሳደግ  በሚችሉባቸው  ጉዳዮች  ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

በተጨማሪም መሪዎቹ የጋራ በሆኑ የተለያዩ ጉዳዮች ላይም ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል ።

የኳታሩ  አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀመድ አልሳኒ  በ2008 ዓመት  ሚያዚያ ወር  ላይ  በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው  ይታወሳል ።

አሚሩ በጉብኝታቸው ወቅትም በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝም ፣ በኢንቨስትመንትና የመሠረተ ልማት ግንባታን ጨምሮ   ኢትዮጵያና ኳታር  በ11  ዘርፎች በጋራ ለመሥራት  ስምምነት ፈጽመዋል ።( ምንጭ: ገልፍ ታይምስ )