ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈው ስብሰባ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የከፈተ ነው

የአገር ውስጥም ሆነ  ከውጭ አገር የተጋበዙ  ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሳተፈው ስብሰባ አዲስ  የፖለቲካ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን  የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ወይዘሪት ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ ።

የፓርቲዎቹ  ስብሰባ የተቃዋሚ ኃይሎች  ከተቃርኖ ይልቅ  አዲስ የፖለቲካ  ምዕራፍ  እንዲከፍቱ በማስቻል  የጎላ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን  ወይዘሪት  ብልለኔ  ገልጸዋል ።

ማክሰኞ  የተካሄደው  የፖለቲካ ፓርቲዎች  ስብሰባ በአገሪቱ  አዲስ  ለተጀመሩትን   የደሞክራሲ ምህዳርን የማስፋት  እንቅስቃሴ አጋዥ እንደሚሆንም  ተገልጿል ።

ለወደፊቱም   የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  አሁን  የተጀመረውን   የፖለቲካ  ፓርቲዎች   ውይይት አጠናክሮ  በማስቀጠልም  ወደ የተሻለ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም  ተናግረዋል  ።

መንግሥት ጎን ለጎን  ከውጭ ከመጡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ትጥቅ ያልፈቱትን  ትጥቅ  እንዲፈቱ  ለማድረግ  የሚወስደውን  እርምጃም እንደሚቀጥልበትም  ስክሬተሪያቷ  ተናግረዋል ።

 ባለፉት  ጥቂት   ወራት  ውስጥ   በሙስና በሰብዓዊ  መብት  ጥሰትን  በተመለከተ  እየወሰደ  ያለው  እርምጃም አንድን  ወገን ወይም  ብሔር ላይ ያተኮረ  አለመሆኑን የገለጹት  ሴክሬተሪያቷ በአቃቢ ህግና በፀረ-ሙስና ኮሚሽኑ እየተካሄዱ ያሉትን  እርምጃዎች  ተጠናክረው  መቀጠል ይተባቸዋል ብለዋል ።

በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችና ሁከቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ  ከማድረግም ባሻገር  አጥፊዎችን  ለፍትህ በማቅረብ   የህዝቦችን  ሰላም  ለማስፈን  አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም  በመግለጫው ተመልክቷል ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ  ዘላቂ ሰላም  ለማስፈን በምታደርገው ጥረትም የዓለም አቀፍ  ድጋፍን  እያገኘችና  በአህጉሩ ያላትን ተጽዕኖና ተቀባይነትም እያሳደገች መምጣቷን ሴክሬተሪያቷ  ተናግረዋል ።