በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋት የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎችን የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጸዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ትላንትና በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ፖሊስን ጨምሮ በአካባቢው የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ አዲሱ በፅሑፋቸው አስፍረዋል፡፡